ከአፋረኛ የተተረጎሙ ተረትና ማሌዎች

ተረት፤ ተረት መምሰል አለበት፤ ልጅ አባት መምሰል አለበት

ሙገሳ ገደል ያስገበሃል፤ የሰው  ምክር ሜዳ ላይ ያስቀራሃል

በሌሊት የጀመሩት ጉዞና በልጅነት የወለዱት ልጆች ለጥሩ ግዜ ያደርሱሃል

ቤት ጭንቅላት ይዳብቃል እንጅ ወሬ አይደብቅም 
ጎረ ቤት አይወርሲም ያስወሪሳል እንጂ
እራሱ ቤት ወተት የደፋ፣ በሰው ቤት ውሃ ይዳፋል 
አንተን ካስመሰሉህ የመይመስልህ ነገር የለም 
የሌባ አፍ ትኩስ ነው ፤መቀመጨህ ቀዝቀዛ ነው 
ያልወለደ የልጅ ጣእሚና አያውቅም፣ አደንጋሊታ ዛፍ የዝናብ ታእሚና አታውቅም
አገሩን የማያውቅ ሰው መሬት እየረገጠ መሬትን ይረግማል
ከአባት የወረሰውን ሀብት የሚያጠፋ ልጅና ከአባት የልወረሰውን ሀብት የሚያካብት ልጅ አለ 
የዚች አለም ኑሮ ያመቻቸህለት ልጅ የሰማይ ቤትህን ያመቻችለሃል 
አንተ የሚታውቆውን ነገር የሚያውቅ ሰው እንጄራ አያስበስልህም
ምጥ የያዛት ሴት ሞት ሊጠረጠር ይችላል የአዋላጅ ሴት ሞት ግን አይጠረጠሪም 
ትልቅ ሰው ተቃምጦ ያየው ትንሽ ልጅ በቁሙ አያይም
አባት ለልጅ ህመም የሚጔዘው ርቀት ልጅ ለአባቱ አይጔዝም 
ጅል ጋር ያደረጉት ንግግር በአሻዋ ላይ እነደ ሸናህ ሽንት ነው
የኬኬ ጨዋታና የቤት ውስጥ ጠብ ለማንም አይከብድም 
ሆድ ከታተሙ በጀርባ ይታኛሉ፤ ራስ ከታተሙ ራስን በሻሽ ይታሰራሉ 
ከመጥፎ አዋላጅ የማዋላጃ ማሳሪያ ይበላሻል፤ካለማወቅ ማበጠሪያ ይበላሻል 
ንግግር መንገድ አለው ፤ ቤት ማውጫ አለው
ንግግርን ወይ መቻል ነው፤ ወይ መራቅ ነው
ቃል አይካዲም፤ ማዋለጃ ቢላዋ አይዋጥም 
መናገር የሚጠበቀው ሰው እያለ፤ ለመናገር የሚቾኩሉ ሰዎች አሉ 
ንግግር ከለ እውነት አይሆንም፤ እውነትን ግን አይወዱትም
መውለድን የሚያስረግም ልጅ ይወለዳል፤ ዝናብ መምጣትን የሚያስጠላ ዝናብም ይዘንባል 
አይመስለቸውም እንጅ ጠንከራ ደካማ የሚሆንበትን ግዜ ቅርብ ነው 
አልሄድ ያለው የፊተኛው ግመል ሆኖ እያለ የሚመታው ግን የኋለኛውን ግመል ነው 
ከጎረ ቤት አመል ይወረሳል፤ከ የኋለኛውን ግመል ነው 
ሳያዩት አያውቁም፤ ሳያኚኩ አይዉጡም የኋለኛውን ግመል ነው 
ሀብታም ሰው የሚለፋ አይመስላቸውም፤ መሃን የሚካሳ አይመስላቸው