ባህላዊ ዘፈንና ጭፈራዎች:


ሆራ / Horra:


የአፋር ባህላዊ አጨ ዋወት ዘፈንና ጭ ፈራው አይ ነቱ የበዛና የሰፋ ቢሆንም በዋ ነኛነት የሚ ታወ ቁት በሰርግ፤ በሃይማኖታዊና ማህበራዊ በአላት እድ ሜና ጾታን በመለየት እንዲሁም ሁሉም በጋራ ተሳትፎ የሚያደርጉበት አንኳር የአጨዋወት ስልት መታወቂያዎች እንደሚከተለው ይ ገልጻሉ፡፡

1. ሆራ ፡- ከድሮ ጀምሮ የመጣ ባህላዊ ዘፋን ነው ፡፡ 

ጨዋታዉ የሚጨ ወቱ ወንዶች ብ ዛታቸው ከስድ ስት ማ ነስ የለባቸውም ፡፡

መ ጀመ ርያ ጨ ዋታ ዉን የመ ጀሚ ረው ከወንድ ነው፡፡ አጨወወቱም ፡ –

ጊሌ በቀኝ እጅ ይያዛል፤ ከዚያ እግር መንሳት ይጀምራ ል፤ የሁሉም እግር በእኩል አነሳስ አለው፡፡ 

እግር በጉልበት ላይ በመታጠፍ እስካ መቀመጫ ይነሳል፡፡ ጨዋታው ወደ ጦርነት ሲኬድ፤ በኢድ፤ በሰርግ ወዘተ ጊዜ ይጨዋሩታል ፡፡

ሰደአ፡- / Sadda’a


ሰደአ የሚባለው ደግሞ ሁሉንም ጾታዎች የሚያሳትፉ ቢሆንም ልጃገረዶች ብቻቸውን የሚጨፍሩበት እንዲሁም ለአካለመጠን የደረሱና ከዚያም በላይ የሆኑ ግን ከጾታ ተቃራኒያቸው ጋር አብረው መጫወት የሚችሉበት የጨዋታ አይነት ነው ፡፡

ትርትራ፡ /Tirtira


ትርትራ የሚባለው ለጦርነት ሲሄዱና ድል አድርገው ሲመለሱ የጀግንነት ስሜት የሚገልጹበት አንድ ፉከራና ቀረርቶ ዓይነት አጨዋወት ሲሆን አብዛኛው በጎሳ ጎሳዎች በእድሜ በሰል ብለው በሚገኙ ሰዎች ዘንድ ይታወቃል፡፡

ላሌ፡-/ Laale


ላሌ በመባል የሚታወቀው ጨዋታ በየትኛውም የበዓል ጊዜ የሚዘፈንና በተቀባባይ አቀንቃኝ /ዘፋኝ / እድሜ ሳይለይ ወንዶች ብቻ የሚጨፍሩበት በድምጽ በጭብጨባና በእግር ዝላይ እንቅስቃሴ ይታጀባል፡፡

ኬኬ:- / Keeke


ኬኬ በመባል የሚታወቀው ጨዋታ በየትኛውም የበዓል ጊዜ የሚዘፈንና በተቀባባይ አቀንቃኝ /ዘፋኝ/ እድሜ ሳይለይ ወንዶች ከሴቶች ጋር የሚጨፍሩበት በድምጽ በጭብጨባና በእግር ዝላይ እንቅስቃሴ የታጀበ የጨዋታ አይነት ነው፡፡

መላቦ:- Malaabo


መላቦ ጨዋታ ወንዶችን የሚያሳትፉ ሳይሆን ሴቶች ብቻቸውን በመሆን አብዛኛውን ጊዜ በሰርግና በኢድ በአል ጊዜ በተቀባባይ አቀንቃኝ እና በሁለት ረድፍ ተሰልፈው ጊሌ /ሰይፍ / በመያዝ እንደቦታው ስፋትና ጥበት የመዞር እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚጫወቱበት የጨዋታ አይነት ነው፡፡

ከዚህ በላይ የተጠቀሱት አበይት የብሄረሰቡ ባህላዊ የዘፈንና የጭፍራ ዓይነቶች በመጠኑም በሆነ ለማስተዋወቅ እንጂ በእያንዳንዱ ዘርፍ በተለያዩ መጠሪያ የሚጠቀሱ አያሌ የአጨዋወት ስልቶች መኖራቸውን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡

 

ኮዕሶ፤ /ኳስ


ኮዕሶ፤- ከተለያዩ ጎሳዎች በተውጣጡ በሁለት ተቃራኒ ቡድኖች መካካል የሚካሄድና ጉልበትንና ትንፋሽን የሚፋታትን ሲሆን በተጨማሪም ፈጣን ሯጭ መሆን የሚፋልግ እድሜያቸው ከ 18-27 የሚገኙ ወጣት ወንዶች የሚጨወቱት የጨዋታ አይነት ነው፡፡ የጨዋታ ግዜ በበአል ቃናት፤ በስርግ፤ በመኸር ወቅት ወዘተ ነው፡፡ መጨረሻ የእለቱን ጨዋታና ውድድር በመከታተል የሀገር ሽማግሌዎች አሸናፊውን ቡድን በመለየት ውጤቱን የበስራሉ፡፡ ባህላዊ የኮዕሶ ጨዋታ